Skip to main content
Ministry of National Strategyየብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር

28ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ

Climate · posted November 2023

28ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ከ150 በላይ አገራት መሪዎች፣ ከፍተኛ ልዑካን ቡድኖች፣ ሲቪል ማኅበራትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በሚገኙበት ዛሬ ዱባይ ውስጥ በተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ሊቀመንበርነት ይጀመራል። ለኹለት ሳምንት የሚቆየው ጉባዔ፣ አገራት ታዳሽ ካልኾኑ የኃይል ምንጮች ወደ ታዳሽ የኃይል ምንጮች በፍጥነት ሊሸጋገሩ የሚችሉበትን ዕቅድ ይነድፋል። የአገራት የካርበን ልቀት መጠን፣ ታዳሽ ካልኾኑ የኃይል ምንጮች የመውጣት ቃል ኪዳኖችና የበለጸጉ አገራት ለታዳጊ አገራት መከፈል ያለባቸው የአየር ንብረት ለውጥ የጉዳት ካሳ ፥ እንዲሁም የሚሰጡት የገንዘብ ድጋፍ ዋናዎቹ አጀንዳዎች እንደሚኾኑ ይጠበቃል። ከዚህ ጎን ለጎን ሃገራት የሰሯቸዉን የአየር ንብረት ለውጥ ስራዎችን ያቀርባሉ። ኢትዮጵያም ባሏት ሁለት ፓቪሎኖቿ የተለያዩ ሁነቶችን ታስተናግዳለች ።የመሪዎቹ ጉባዔ የሚካሄደው ዓርብና ቅዳሜ ነው።