Skip to main content
Ministry of National Strategyየብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር

ኢትዮጵያ በቡድን 77 አባል ሀገራት እና በቻይና የመሪዎች ጉባኤ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀች።

Climate · posted December 2023

ኢትዮጵያ በቡድን 77 አባል ሀገራት እና በቻይና የመሪዎች ጉባኤ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠየቀች።

ዱባይ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (የፕ.ል.ሚ)

በቡድን 77 እና በቻይና የመሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ የአየር ንብረት ቀውሱን እና በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚፈጥረውን ያልተመጣጠነ ተፅዕኖ ለመቅረፍ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ የአየር ንብረት ለውጥ በከፍተኛ ደረጃ ድርቅና የጎርፍ አደጋ በማስከተል ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ያለውን አስከፊ ጉዳት አመላክተዋል። ሚኒስትሯ አያይዘውም የበለፀጉ ሀገራት የአየር ንብረት ፋይናንስ አቅርቦትን እና ኢንቨስትመንቶችን በታዳጊ ሀገራት ዝቅተኛ የካርቦን እና የአየር ንብረት ለውጥን በሚቋቋም ሽግግር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

የአየር ንብረት ለውጥ ቀውሱ ዓለም አቀፋዊ አደጋ በመሆኑ ዓለም አቀፍዊ ምላሽ ያስፈልገዋል ያሉት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ የአየር ንብረት ተጽዕኖዎችን ለመከላከል እና እርምጃ ለመውሰድ የበለጸጉ ሀገራት ተባብረው ለመላመድ እና የመቋቋም አቅምን ለመገንባት የሚያስፈልጉንን ሀብቶች ማቅረብ አለባቸው ብለዋል፡፡

ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ የሚያስፈልጋቸውን ፋይናንስ እንዲያገኙ የአለም የፋይናንስ አርክቴክቸር ማሻሻያ እንዲደረግ አሳስበዋል። ዓለም አቀፉን የታክስ ሥርዓት ለመለወጥ ለአፍሪካ ግሩፕ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስፈላጊውን የውሳኔ ሃሳብ እርምጃ እንደ ምሳሌ ጠቁመዋል።

ለወደፊቱም በዘላቂነት በተረዳንበት መንገድ ጥልቅ ለውጥ ለማምጣት መስራት አለብን ያሉት ሚኒስትሯ እንደ ቡድን በአንድነት ቆመን የጋራ ድምጻችንን ማሰማት አለብን ነው ያሉት፡፡

የቡድን 77 አባል ሀገራት እና የቻይና የመሪዎች ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ሲካሄድ በአይነቱ የመጀመሪያው ሲሆን በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በጋራ ተግዳሮቶቻቸውን እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የሚወያዩበት እድል እንደሚኖር ማወቅ ተችሏል።

የቡድን 77 አባል ሀገራት እና የቻይና የመሪዎች ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥን ትግሉን ለማራመድ ወሳኝ አጋጣሚ ነው። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ፍፁም አሰፋ አስቸኳይ እርምጃ አለም ሰምቶ እና ተረድቶ ሁሉም ቀጣይነት ያለው እና የማይበገር የወደፊት ህይወት ለመገንባት በጋራ መስራት እንደሚጠበቅ ተገልፃል።